መባዕ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ባጸደቀው የደንበኛ ሳቢ መግለጫ (Prospectus) እና በተሰጠው ፈቃድ መሠረት 200,000 አዳዲስ መደበኛ አክሲዮኖችን የአንዱ ዋጋ በብር 550.00 (አምስት መቶ ሃምሳ) ለሽያጭ ማቅረቡን በደስታ ይገልጻል። የሽያጭ ማቅረቢያ ጊዜው ከነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ኅዳር 05 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ከAugust 17, 2026 እስከ November 14, 2026) ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
በደንበኛ ሳቢ መግለጫው (prospectus) ላይ በተገለጸው መሠረት፣ አዳዲሶቹ አክሲዮኖች ለነባር ባለአክሲዮኖች የሚደለደሉት ባላቸው የድርሻ መጠን (pro rata basis) መሠረት ይሆናል። ማይክሮፋይናንሱ ሳይሸጡ የቀሩ ማናቸውንም አክሲዮኖች ተጨማሪ አክሲዮን ለመግዛት ፍላጎት ላላቸው ነባር ባለአክሲዮኖችና ለአዳዲስ ኢንቨስተሮች ይሸጣል። የመግዛት ፍላጎት ያላችሁ ነባር ባለአክሲዮኖችና አዳዲስ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸዉ የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ደላላዎች (Securities brokers) የግብይት ሂሳብ (trading account) በመክፈትና የግዢ ትዕዛዝ በመስጠት የአክሲዮን ግዥውን እንድትፈጽሙ ማይክሮፋይናንሱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ባለአክሲዮኖች/ኢንቨስተሮች የሚከተሉትን አስፈላጊ ሰነዶች ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፦
- የፋይዳ (National ID) መታወቂያ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
- የኢሜይል አድራሻ እና የስልክ ቁጥር
- በተወካይ አማካኝነት የሚፈጸም ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃ
⚠️ ማሳሰቢያ
በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የጸደቀው የደንበኛ ሳቢ መግለጫ (Prospectus) እና ተያያዥ ሰነዶች በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ባለአክሲዮኖች እና አዳዲስ ኢንቨስተሮች የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን በሙሉ እንዲያነቡት ይበረታታሉ። ለውሳኔ ከተቸገሩ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ግዥ ከመፈጸምዎ በፊት በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸውና ገለልተኛ የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ምክር ይጠይቁ። የደንበኛ ሳቢ መግለጫው በባለሥልጣኑ መጽደቅ ሰነድ ሙዓለ ንዋዮችን ባለሃብቶች እንዲገዙ የተሰጠ ምክር ወይም ድጋፍ አይደለም። ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ አግኝቷል።